Kaufland
ከመስራች ኩባንያ መርሆቻችን አንዱ "የሚመለከታቸውን ህጎች እና የውስጥ መመሪያዎችን እናከብራለን" (ተገዢነት) የሚለው ነው። ህጋዊ ተገዢነት በሚያረጋግጠው አሰራራችን ሊያምኑን እንደሚችሉ እናረጋግጣለን። በሌላ አገላለጽ፣ ተገዢነት ቀጣይነት ባለው የኩባንያችን ስኬት ውስጥ ወሳኝ አካል ነው።

ስለዚህ፣ ሊከሰቱ የሚችሉ ስህተቶችን በቀጥታ እና በተቻለ ፍጥነት መከላከል ለእኛ አስፈላጊ ነው። ይህንንም በመጀመሪያ ደረጃ ስለተፈፀሙ ስህተቶች ሪፖርቶችን በመቀበል ማሳካት እንችላለን። በሁለተኛ ደረጃ፣ ኩባንያውን በሚመለከቱ የተገዢነት ጉዳዮች ላይ ምክር የማግኘት እድል እንሰጥዎታለን።

ለዚህ አላማም የመስመር ላይ የጥቆማ ስርዓት ዝግጁ ነው። ስርዓቱን መረጃ ለመስጠትም ሆነ መረጃ ለማግኘት ቢጠቀሙበትም: መረጃዎ በከፍተኛ ሚስጥራዊነት የሚያዝ ሲሆን ከፈለጉም ስምዎ ሳይጠቀስ ይያዛል። ሪፖርትዎ ላይ ጥያቄዎች ካሉን ልናገኝዎ እንድንችል የመልዕክት ሳጥን እንዲያዘጋጁ እንመክርዎታለን። በBKMS በኩል ሪፖርት ከላኩልን፣ በጥቆማ ሰጪዎች ጥበቃ ህግ (Whistleblower Protection Act) መሰረት ሙሉ ጥበቃ ያገኛሉ።

እባክዎ ይህንን የመስመር ላይ የጥቆማ ስርዓት በሃላፊነት ይጠቀሙ። ሌሎች ሰዎችን ለመወንጀል አላግባብ ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። ስለዚህ፣ በእውቀትዎ እና በእምነትዎ ትክክል ነው ብለው የሚያምኑትን መረጃ ብቻ ሊሰጡን ይገባል።

ይህ የመስመር ላይ የጥቆማ ስርዓት የተቋቋመው ከተገዢነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ሪፖርት ለማድረግ ነው። እባክዎን ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ስርዓት ሊገቡ እንደማይችሉ ልብ ይበሉ።

ይህ የመስመር ላይ የጥቆማ ስርዓት ቢኖርም፣ ሪፖርቶችን ለማቅረብ ወይም ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ሌሎች መንገዶች (ለምሳሌ የተገዢነት መኮንኖች) እንደተጠበቁ ናቸው።
ለምን ሪፖርት አቀርባለው?
የኦንላይን ሪፖርት ማድረጊያ ሥርዓት መጠቀም የትኞቹ ጉዳዮች ሊፈቱ ይችላሉ?
ስጋትን ሪፖርት ለማድረግ ወይም ጥያቄን ለመጠየቅ ሂደቱ ምንድ ነው፣ እንዴት የፖስታ ሳጥን ማዘጋጀት እችላለሁ?
መቼ እና እንዴት ነው ኣስተያየት የምቀበለው?
የኦንላይን ሪፖርት ማድረጊያ ሥርዓት ስጠቀም የእኔ መረጃ እንዴት ይጠበቃል?